Logo

ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ ምን እያደረጋችሁ ነው?

By Abenezer FikaduJune 23rd, 2025

እርሱ ኢየሱስ የቱ እንደ ሆነ ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ነገር ግን ቁመቱ አጭር በመሆኑ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሊያየው አልቻለም። ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ዘኬዎስ እርሱን ለማየት ብሎ ከሕዝቡ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። (ሉቃስ 19:3–4)

ዘኬዎስ ይሄ የሚያደርገው ነገር በሰዎች ዘንድ የሚያስመስለው ነገር ግድ አልሰጠውም።

ሀብታም ሰው ነበር። የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ። ሰዎች የሚጠሉት ዓይነት ሰው። ሆኖም ኢየሱስ ወደ ከተማ ሲመጣ፣ ሕዝቡን ጥሶ እንደ ልጅ ዛፍ ላይ ወጣ፣ ዝም ብሎ ለማየት።

ለምን?

ምክንያቱም የሆነ ነገር ውስጡ ኢየሱስን እጅግ ይፈልግ ነበር። ያ ጥማት እፍረትን አስረስቶት ነበር። ማዕረጉን፣ የሰዎችን እይታ አልፎ።

ሕዝቡ እስኪበተን አልጠበቀም። የግል ግብዣም አልፈለገም። ራሱን ከኢየሱስ ጋር ሊያገናኝ በሚችል ቦታ ላይ አስቀመጠ።

ዋናው ቁም ነገርም ይሄው ነው።

ዘኬዎስ የወጣው ምን እንደጎደለው ስለሚያውቅ ነው። ገንዘብ የሚገዛው ነገር ሁሉ ነበረው፣ ግን ኢየሱስን በገዛ ዓይኑ ማየት ነበረበት።

አሁን ከባድ ጥያቄ ይኸውና:

ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ ምን እያደረጉ ነው?

እውነቱ ደግሞ ይሄውና፦

መርሃግብርዎ በጣም የተጨናነቀ ከሆነ፣ ስልክዎ ትኩረት የሚከፋፍል ከሆነ… እርሱን በሕዝቡ መካከል ያጡታል።

ግን በእውነት ማደግ ከፈለጉ? በእውነት ከእርሱ ጋር መሄድ ከፈለጉ? እርስዎም መውጣት ያስፈልግዎታል።

ከዚህ ይጀምሩ:

ነገ 30 ደቂቃ ቀድመው ይንቁና ከወንጌል አንድ ምዕራፍ ብቻ ያንብቡ። ጎላ ያሉትን ነገሮች ምልክት ያድርጉባቸው። ያ የእርስዎ ዛፍ ነው።

በየቀኑ ስልክ የሌለበት፣ ጸጥ ያለ ቦታ ያግኙ። ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ። ያዳምጡ። በየቀኑ አንድ የተማሩትን ነገር ይጻፉ።

በዚህ ሳምንት ከአንድ ነገር ይጹሙ። የማህበራዊ ሚዲያ፣ ስኳር፣ ወይም ማጉረምረም ሊሆን ይችላል። ያንን ጊዜ በመጸሐፍ ቅዱስ ንባብ ወይም በጸሎት ይተኩት።

ኢየሱስ ዘኬዎስን ያየው ስለወጣ ነው። እግዚአብሔርን ማስደመም አያስፈልግዎትም። ዝም ብለው መቅረብ እና ከትናንትናው ከፍ ብለው መድረስ ብቻ ነው የሚያስፈልገው።